This blog post is in Amharic, if you are seeing boxes download fonts here.
ይህ ዶኪመንቴሽን በዳሌ ወረዳ በፍራፍሬ ማዳቀልና የችግኝ አቅርቦት ኤክስቴንሽን ይዞ የቀረበ ነው፡፡ በዳሌ ወረዳ ያሉ አርሶ አደሮችና የወረዳው ግብርና ከመልካሳ የግብርና ምርምር ጣቢያ እና ከ IPMS (በኢትዮጵያ ምርታማነትና የገበያ ስኬት ማሻሻያ) ፕሮጄክት ጋር በመሆን የአቮካዶ፣ የማንጎና ሌሎች የፍራፍሬ ዝርያዎችን ለማልማትና ምርታማነትን ለማሻሻል የጋራ እንቅስቃሴ ፈጥረዋል። በዚህም እንቅስቃሴ አዳዲሰ የማንጎና የአቮካዶ ዝርያዎችን በማደቀል አስተዋውቀዋል። በተጨማሪም እነኚህን አዳዲስ ችግኝ ማዳቀልና ማፍላት በወረዳው ለተመረጡ ገበሬዎች ከመልካሳ የግብርና ምርምር ጣቢያ በመጣ አሰልጣኝ ድጋፍ ስልጠና ተሰጥቷል። ይህ ዶኪመንቴሽን ቪዲዮ በዳሌ ወረዳ የፍራፍሬ ልማት የአርሶ አደሩን ተሞክሮና ስኬቶችንም አካቶ ይዟል።