Amharic / East Africa / Ethiopia / Event / ILRI40 / Livestock

ኢልሪ (ILRI) 40ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው: የቁም እንስሳት ዘርፍን ኢኮኖሚያዊ ድርሻ ለማሳደግ እየተሠራ ነው

This blog post is in Amharic, if you are seeing boxes download fonts here.

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎ ርሜሽን ዕቅድ ኢትዮጵያ ከቁም እንስሳት ሃብቷ ተገቢውን ጥቅም ለማግኘት ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች፡፡

ዓለም አቀፉ የቁም እንስሳት ምርምር ኢንስቲት ዩት (ILRI) የተመሰረተበትን አርባኛ ዓመት በአዲስ አበባ በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሥነ ስርዓቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከቁም እንስሳት የሚገኘውን ገቢ ከማሳደግ በተጨማሪ ለአገሪቱ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ የሚጫወተውን ሚና ማሳደግ ይገባል፡፡ የቁም እንስሳት ሃብት ለአጠቃላይ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት፣ ድህነት ቅነሳ እንዲሁም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡ ለዚህም በቀጣዮቹ ዓመታት የተጠናከረ ስራ ማከናወን ይገባል፡፡

«በበርካታ የልማት ማነቆዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም አላገኘችም» ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቁም እንስሳት እና ስጋ ሽያጭ ከቀጥተኛ የወጪ ንግድ ገቢ ታገኝ የነበረው 262 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ሲሆን ሃብቱ ግን ከዚህ የላቀ ገቢ ማስገኘት እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም በመሰረተ ልማት፣ በገበያ ስርዓት፣ በእንስሳት ጤና፣ በእንስሳት ጊዚያዊ ማቆያ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ይሰጣል፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወቅት በዘርፉ እሴት በመጨመር ለድህነት ቅነሳ ተግባር ሚና ይኖረዋል፡፡

አርባኛ ዓመቱን የሚያከብረው ዓለም አቀፉ የቁም እንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ኢልሪ) በአቅም ግንባታ እና ፕሮግራም ማስተባበር ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ለቀጣዩ አስር ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ የቁም እንስሳት ልማት መሪ ዕቅድ በተያዘው ዓመት እንደሚተገበር አቶ ደመቀ አስታውቀዋል፡፡

HE Teferra Derebew, Minister of Agriculture, Ethiopia

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው ከግብርና ውጤት ገሚሱን የሚሸፍነው የቁም እንስሳት ንዑስ ዘርፍ ያሉበትን ማነቆዎች በማቃለል በቀጣይ እንደሚያድግ የሚጠበቀውን የአገር ውስጥ የወተት እና ሥጋ ፍላጎት ለማሟላት አቅሙን ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡ እ..አ ከ1974 ጀምሮ በኢትዮጵያ ስራውን የጀመረው ኢልሪ ባለፉት ዓመታት በእንስሳት አመጋገብ እና ጤና አጠባበቅ፣ በአርብቶ አደሩ፣ በእሴት ሰንሰለት፣ በመሬት አጠቃቀምና ሌሎች ቁልፍ ተግባራት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶች ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡

ለግብርና ልማት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ፕሬዚዳንት ካናዮ ንዋንዜ እንዳሉት፤ በቀጣዮቹ ሁለት አሰርት ዓመታት የዓለም የምግብ ፍላጎት በእጥፍ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የቁም እንስሳት ሃብት ያላቸው አገራት ኢንዱስትሪው የሚፈጥርላ ቸውን መልካም እድል መጠቀም ይገባቸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሄድ ኮንፈረንስ አርባኛ ዓመቱን የሚያከብረው ኢልሪ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የሚያደርጉ ባለሙያዎችን ጋብዟል፡፡

ባለፉት አራት አሰርት ዓመታት በተለያዩ አፍሪካ አገራት በፖሊሲ፣ በገበያ፣ በቁም እንስሳት እና ዓሣ፣ በምግብ ዋስትና እና በዓየር ንብረት ለውጥና ተያያዥ ዘርፎች ምርምር ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ከአዲስ ዘመን የተወሰደ

ሌላ የዜና ጥንቅሮች:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s